የነገ ትውልድ ተስፋ አረንጓዴ ልማትና ቱሪዝም
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አረንጓዴ ዐሻራ ሥነ ምሕዳርን እና የተፈጥሮ ሃብትን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ ዘላቂ የልማት ሒደት ነው።
በአሁኑ ወቅት የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ ብክለት ዓለማችንን ከቀን ወደ ቀን እየተፈታተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ናቸው።
በዚህ ወሳኝ ሰዓት የኢኮኖሚ እድገትን ከእውቀትና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ማጣጣም አማራጭ የሌለው ተግባር ሲሆን ÷ መርሐ ግብሩ የቱሪዝም ዘርፉ ዘላቂ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
አረንጓዴ ዐሻራ ደንን፣ እንስሳትን፣ ዕፅዋትን፣ ፓርኮችን እና ውብ መልክዓ ምድሮችን ከጥፋት በመታደግ ለቱሪስቶች ማራኪ እንዲሆኑ ያስችላል።
የካርበን ልቀትን በመቀነስ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን እንደ ታዳሽ ኃይል እና አረንጓዴ ሕንፃዎችን በሆቴሎችና ሎጆች በመጠቀም የቱሪዝም መስሕብን ያሰፋል።
ሀገራችን ለአካባቢ ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት በማሳየት ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን መሳብ ችላለች።
ቱሪዝም የአካባቢ ማሕበረሰብን ተጠቃሚ በማድረግ የተፈጥሮ ሀብቱን ጠባቂ እንዲሆን ያነሳሳል።
እንዲሁም የአካባቢውን ባህላዊ እሴቶች፣ ወጎች እና ታሪካዊ ቅርሶች በመንከባከብ ትክክለኛ እና ዘላቂ የቱሪዝም ተሞክሮ ይፈጥራል።
አረንጓዴ ዐሻራ እና ቱሪዝም የትኛውንም ሀገር ኢኮኖሚ ከፍ የሚያደርጉ፤ ለመጪው ትውልድ ንፁህ እና ውብ ዓለም ለማስረከብ የሚያስችሉ ተግባራት ናቸው።
ቱሪዝምን እና የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴን በዕቅድና በቁርጠኝነት ማቀናጀት የነገዋን የበለፀገች እና ጤናማ ዓለም ማረጋገጫ ዋስትና ነው።
በትዕግስት ግዛቸው