Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከታ የሆነ አስተማማኝ የመከላከያ ሠራዊት ተገንብቷል – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በአስተማማኝነት የሚጠብቅ የመከላከያ ሠራዊት ተገንብቷል አሉ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ45ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን “ጽናት ኮርስ መሠረታዊ ኮማንዶዎችን” በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአየር ወለድና ኮማንዶ ኃይል በአካል ብቃቱ፣ በጽናቱና በከፍተኛ ወታደራዊ እውቀቱ የውጊያ አቅጣጫ ቀያሪ ኃይል መሆኑን ተናግረዋል።

የአየር ኃይልና ኮማንዶ ኃይል አስቸጋሪ ፈተናዎችን ውስጥ አልፎ ሀገራዊ አደራውን በብቃት መወጣቱንም ገልጸዋል።

ተመራቂዎቹ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በታማኝነትና በቁርጠኝነት ማስከበር የሚችሉ ዝግጁ ኃይል በመሆን በተለመደው ጀግንነት ሀገራቸውን እንዲጠብቁም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መከታ የሆነና በዘመናዊ ትጥቆች የተደራጀ አስተማማኝ የመከላከያ ሠራዊት ተገንብቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ዛሬም በአስተማማኝ ዝግጁነት ላይ እንገኛለን ሲሉም ነው የገለጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.