ማንቼስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል በአዲስ አሰልጣኝ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል በአዲስ አሰልጣኞች ዛሬ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ማንቼስተር ሲቲ በቀድሞ የቼልሲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ እየተመራ ቀን 10 ሰዓት ላይ ከበርንማውዝ ይጫወታል።
ቡድኑ ከ10 ዓመት በኋላ ያለ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚያደርገው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
በሌላ በኩል አሰልጣኝ አርነ ስሎትን ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ አሰናብቶ አንዶኒ ኢራኦላን የሾመው ሊቨርፑል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ተጉዞ ኒውካስልን አመሻሽ 12:30 ላይ ይገጥማል።
እንዲሁም ከዚህ ቀደም ብሎ ብራይተን ከአስቶን ቪላ በዕለቱ 10 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሌላኛው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ነው።
አርብ ዕለት የጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከአሁኑ ጠንካራ ፉክክሮችን እያስመለከተ ሲሆን የአምናው ሻምፒዮን አርሰናል ተጋጣሚዉን በማሸነፍ ሲጀምር ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ በሃል ሲቲ የ2 ለ 0 ሽንፈትን ገጥሞታል።
ከዚህ በተጨማሪ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0፣ ኢፕስዊች ታውን ሰንደርላንድን 2 ለ 1፣ ብሬንትፎርድ ቶተንሃም 3 ለ 0 እንዲሁም ሊድስ ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።