Fana: At a Speed of Life!

76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀመድ አሊ ዩሱፍ ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከ40 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮችና ተወካዮች፣ የዓለም ጤና ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያለፈችበትን ረጅም ጉዞ ለማሳየት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ታምኖበታል፡፡

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.