Fana: At a Speed of Life!

አሰቃቂው የኔፓል የጎርፍ አደጋ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኔፓል በተከሰተው አስከፊ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 177 ሲደርስ፤ ከ800 በላይ ሰዎች ደግሞ የገቡበት አልታወቀም፡፡

በትላንትናው እለት ኔፓል ከቻይና ጋር በምትዋሰንበት የቲቤት ግዛት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በርካታ ቤቶችን እና ድልድዮችን ሲያፈራርስ የበርካቶችን ሕይወትም አጥፍቷል፡፡

በአደጋው እስካሁን 177 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ800 በላይ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ እና የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል የኔፓል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የወንዝ ዳር ከተማ የሆነችው ቲቤት የጂኦግራፊ አቀማመጥ እና በከተማዋ የተከሰተው የማያቋርጥ ዝናብ የነፍስ አድን ስራዎችን ለማከናወን አስቸጋሪ እንዳደረገውም ተመላክቷል።

በአደጋው ከኔፓል ዜጎች በተጨማሪ የሕንድ፣የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተወጣጡ ከ100 በላይ ቱሪስቶች ህይወታቸው አልፏል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እንዳስታወቀው በኔፓል የጣለው ከባድ ዝናብ የበረዶ ግግሮች እንዲፈርሱ በማድረግ ለአደጋው መፈጠር ምክንያት ነው፡፡

አደጋው ሲከሰት የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ትላንት ምሽት በበርካታ ማህበራዊ ድህረ ገፆች የተጋራ ሲሆን ለኔፓል የነፍስ አድን ስራ በርካታ ሀገራት የእርዳታ ልዑክ እያሰማሩ ነው መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.