ሊቨርፑል ብረድሊ ባርኮላን ከፒኤስጂ ለማስፈረም ከስምምነት ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ፈረንሳዊውን የግራ ክንፍ ተጫዋች ብራድሊ ባርኮላን ከፒኤስጂ ለማስፈረም ከስምምነት ደረሰ፡፡
ሊቨርፑል የ23 አመቱን ተጫዋች በ100 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ አንፊልድ ለማምጣት ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር ከስምምነት ደርሷል፡፡
በፈረንጆቹ 2023 ከሊዮን በ38 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ፓሪስ የደረሰው ባርኮላ ከፒኤስጂ ጋር 3 የሊግ አንድ፣ 2 የሻምፒዮንስ ሊግ እና ሌሎችም ዋንጫዎችን አሸንፏል፡፡
ብራድሊ ባርኮላ በቀጣዮቹ 48 ሰዓታት የሊቨርፑል ተጫዋች ለመሆን መቃረቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡