739 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 14 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገ ክትትል ከ739 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል አለ የጉምሩክ ኮሚሽን ፡፡
የተዙት እቃዎች አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ ጫት፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ናቸው፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ሕብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና ብርበራ ነው የተያዙት፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 25 ተጠርጣሪዎች እና 17 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም የኮሚሸኑ መረጃ አመልክቷል፡፡