የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የዶሮ ሥጋና እንቁላል ምርትን በማሳደግ ዘመናዊ የዶሮ እርባታን እያስፋፋ ነው አሉ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ።
የተሻሻሉ ዝርያዎችን ማስፋፋት፣ ዘመናዊ ማባዣና ማስፈልፈያ ማዕከላትን ማጠናከር፣ የጫጩት እንክብካቤና የባዮ ሴኩሪቲ ሥርዓትን ማሻሻል እንዲሁም የግል ባለሀብቶችን ማሳተፍ የኢኒሼቲቩ ዋና ትኩረቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።
በዚህም አርቢዎችን ከአነስተኛ እርባታ ወደ ገበያ ተኮርና ምርታማ የዶሮ ልማት በማሸጋገር ለምግብ ዋስትና፣ ለገቢ ምንጭና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክት ዘርፍ እየሆነ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ለአብነትም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን፣ ኡራ ወረዳ በሚገኘው “ጸጸ” የዶሮ ልማትና መኖ ማደራጃ ማዕከል የሚካሄደውን የዶሮ እርባታ ሥራ አንስተዋል።