Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀምሯል።

በቢሮው የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፀጋዬ ደበላ እንዳሉት፤ በአዲስ አበባ የዋጋ ንረትን ከመከላከል እና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል።

በአሁኑ ወቅት የፍጆታ አቅርቦት ችግር አለመኖሩን ገልጸው በዓልን እንደ ሰበብ በማድረግ በምርት ላይ አግባብነት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ምርት በሚያከማቹ እና በሚደብቁ ላይ መንግስት አስፈላጊውን ርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የተከፈቱት ባዛሮቹ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች መዘጋጀታቸውን እና በቂ ምርት መቅረቡን ገልፀው የከተማው ነዋሪ በባዛሮቹ ተገኝቶ እንዲገበያይ ጥሪ አቅርበዋል።

የበዓል ባዛሮቹ ከዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጷጉሜን 5 ድረስ ለኅብረተሰቡ ክፍት ሆነው አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን የቢሮው መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.