Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ታላቅ ያደረጋት ሉዓላዊነት የተገነባው በልጆቿ ጽናት ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያን ታላቅ ያደረጋት ሉዓላዊነት የተገነባው በልጆቿ ጽናት ነው አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፡፡

‎ጳጉሜን-3 የጽናት ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

‎ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ያጋጠሟትን ፈተናዎች ተሻግራ ለዛሬ የደረሰችው በሕዝቦቿ የተባበረ የጽናት መንፈስ ነው፡፡

‎ዛሬም እንደታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያሉ የልማት ድሎችን የማስመዝገባችን ምስጢር በፈተናዎች ያለመበገራችንና የጽናታችን ውጤት ነው ብለዋል።

‎ኢትዮጵያ ሉዓላዊትና የተከበረች ሀገር ሆና የቀጠለችው በአንድ ትውልድ ብቻ አይደለም ያሉት አቶ አሻድሊ፤ ይልቁንም በትውልድ ቅብብሎሽ በተሻገረ የአብሮነት ጽናት መሆኑን ገልጸዋል።

‎ዛሬም ከቀደመው ትውልድ የተረከብናትን ከመጠበቅ ባሻገር የበለጠ የተከበረች እና የበለጸገች ሀገር ገንብተን ለትውልድ የማሻገር አደራችንን መወጣት አለብን ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

‎እንደሀገርም ሆነ እንደክልል በየዘርፉ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የተጀመሩ የሰላም፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳድር እና የቴክኖሎጂ ሥራዎችን ለማጠናከር የአሁኑ ትውልድ የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.