Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ህልውና በጋራ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው – አቶ መሐመድ እድሪስ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገርን ህልውና በጋራ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው አሉ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጳጉሜን 4 “የኅብር ቀን”ን በማስመልከት የኪነ ጥበብ ምሽት አካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ህልውናና ጥንካሬ በብዝሃነት፣ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ የጸና ነው፡፡
የቀደሙ አባቶችና እናቶች አብሮነታቸውን አጎልብተው ያቆዩልንን ሀገር በአንድነት ተጠናክረን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ቃላችንን የምናድስበት ወቅት ነው ብለዋል፡፡
የሀገርን ህልውና በጋራ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.