Fana: At a Speed of Life!

የባሕር በር ለኢትዮጵያ ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው ወሳኝ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው ወሳኝ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕንድ ኒውዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪከስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ግዙፍ ኢኮኖሚና ብዙ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ የባህር በርና አስተማማኝ ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ያስፈልጓታል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የባህር በር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጅግ አስፈላጊና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ግዙፍ ኢኮኖሚና ብዙ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባህር በርና ብዝሃ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች እንደሚያስፈልጓት ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ ጥያቄዋ በጋራ ተጠቃሚነትና የጋራ እድገት የተመሰረተ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ብሪክስ የበለጠ ተፅዕኖው የሚጎላው በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ወሳኔ መስጠት ሲችል መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአባል ሀገራቱ እድገትና የወደፊት እጣ ፋንታ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.