የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፉ የአሜሪካ ልማት ተርአዶ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አበረከተ።
ዩ.ኤስ.ኤይድ ኢትዮጵያ በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው፥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ባለበት በዚህ ወቅት ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር የመመርመር አቅመን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ማበርከቱን የገለፀ ሲሆን፥ ድጋፉም የኢትዮጵያን የምርመራ አቅምን ያሳድጋል ብሏል።
የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶቹ አዲስ አበበን ጨምሮ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ በተዛመተባቸው አካባቢዎች እንደሚውልም አስታውቋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።