Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!

የመስቀል በዓል መስቀሉ ለ300 ዓመታት ከተደበቀበት የወጣበት በዓል ነው፡፡ መልካም የምሥራች የተነገረበትና ብርሃን የተገለጠበት በዓል ነው፡፡

በአንድ ዘመን የተሳሳቱ ሰዎች የፈጠሩትን ጥፋት፤ በሌላ ዘመን የተነሡ ተቆርቋሪ ሰዎች አስተካክለውታል፡፡ ልክ እኛ የባሕር በርን ለማስተካከል እንደምንሠራው፡፡

አስቸጋሪ የክረምት ወር አልፎ የመጸው ወር በሚብትበት ጊዜ የሚከበረው መስቀል የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ነው፡፡ በአንድ በኩል ችቦዎች ተደምረው ደመራውን ይገነባሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ሁሉ በተመሳሳይ ቀን፣ በተመሳሳይ አከባበር፤ እንደየብሔረሰቡ ባህል ተደምረው በዓሉን ያከብራሉ፡፡

“የጎመን ምንቸት ውጣ፣ የገንፎ ምንቸት ግባ” እንደሚባለው ሁሉ፣2019 ዓመት፣ አስቀድሞ መውጣት የጀመረው የኢትዮጵያ የችግርና የፈተና ምንቸት ተጠቃልሎ የሚወጣበትና የብልጽግና ምንቸት በየቤታችን የሚገባበት ዓመት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.