ባለፉት 24 ሰዓታት 804 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 20 ሺህ 778 የላብራቶሪ ምርመራ 804 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 55 ሺህ 213 መድረሱንም ሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያወጡት መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈ የ10 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 856 መድረሱንም አመላክተዋል።
በትናንትናው እለት 380 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ 306 ሰዎች ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 283 መድረሱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።