Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  የሠንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን
‎
‎“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን”
‎
‎ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችንና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው።
‎
‎በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል።

አባቶቻችን በፈተናዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ይህ በጋራ የመቆም ጥሪ መቼም ቢሆን ተቋርጦ አያውቅም፤ እያንዳንዱም ትውልድ ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል።
‎
‎መደመር ሁላችንንም አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀናል፤ እኛ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ከዳር ቆመን የምንታዘብ ተመልካቾች ነን? ወይንስ “ይህች ሀገሬ ናት፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም ያሳስበኛል” ማለት የምንችል ባለቤቶች?
‎
‎ቋንቋዎቻችን፣ ሃይማኖቶቻችን እና ማንነቶቻችን ለዘመናት በጋራ በምናልፍበት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ አብረው ተሰናስለው የተሸመኑ የአንድ ሸማ ክሮች ናቸው።

ለሀገር መቆም ከትንንሽ የድፍረት እርምጃዎች ይጀምራል፤ ከራስ አልፎ ሰፊ ርዕይ ይዞ መሥራትንም ይጠይቃል። ያለፉት ትውልዶች ሀገሪቱን እንድንረከብ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ዛሬ በጋራ የምናጸናትን ሀገር ነው ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው።
‎
‎ስለሆነም ዛሬ ራስዎን ይጠይቁ፤ ለሀገርዎ አንድነትና ብልጽግና ምን አበረክታለሁ?

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.