Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፖላንድ በድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ዘርፍ ትብብራቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች፣ እንዲሁም ለተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች የምትሰጠውን የምላሽ አቅም ለማሳደግ ከፖላንድ ጋር አብሮነቷን አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ  የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳደር ኢሎና ኮርቸት ጋር በጤና እና በድንገተኛ አደጋዎች አፈታት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ መድረክ ሁለቱ ወገኖች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ዶ/ር መቅደስ በወቅቱ እንደገለጹት አጋርነቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የድንገተኛ ሕክምና ቡድንን አቅም በስፋት ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

አምባሳደር ኢሎና ኮርቸት በበኩላቸው፣ ፖላንድ የኢትዮጵያን የጤና ተቋማት አቅም ግንባታ እና አጠቃላይ የጤና ሥርዓት ለማጠናከር በድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.