Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ ተቋማትን ማጠናከርና ቅንጅታዊ አንድነታቸውን ማሳደግ ይገባል – የጋና ፕሬዝዳንት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ነባራዊ ሁኔታ እየተቀያየረ ባለበት ሁኔታ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ ተቋማትን ማጠናከርና ቅንጅታዊ አንድነታቸውን ማሳደግ ይገባል አሉ የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማ።
12ኛው የጣና ፎረም የመክፈቻ መርሐ ግብር በውቢቷ ባሕር ዳር በጣና ሐይቅ ዳርቻ “በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ” በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል።
የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጣና ፎረም በአፍሪካ ሰላም፣ ደህንነትና ልማት ዙሪያ በግልጽ የሚመከርበት ነፃ የሃሳብ ገበያ ነው።
በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም መገንባት የሚቻለው በአፍሪካዊ ተቋማትና አፍሪካን በመለወጥ ብቻ ያሉት ፕሬዚደንቱ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ እየተቀያየረ ባለበት ሁኔታ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ ተቋማትን ማጠናከርና ቅንጅታዊ አንድነታቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
ዘላቂ ሰላም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ይጠይቃል፣ መዋቅራዊ ነፃነትን ይፈልጋል፣ ለዚህ ቁርጠኛ መሆን አለብን ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
አፍሪካውያን የአህጉራዊ ኢንዱስትሪ አቅማቸውን ማሳደግ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸው አፍሪካ ራሷን በራሷ መርዳት እና የሰላምና የልማት አጀንዳዎችን በትብብር ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.