Fana: At a Speed of Life!

በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡

በዕለቱ ተጠባቂ ከሆኑት ግጥሚያዎች መካከል በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ከበርንማውዝ ጋር ምሽት 11 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠቃሽ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ሊቨርፑል በሜዳው በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘውን ብራይተን ሆቭ አልቢዮንን ሲገጥም ሃል ሲቲ ከብሬንትፎርድ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከኖው ካስትል ጋር ይጫወታሉ፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ሰንደርላንድ ሊድስ ዩናይትድን በሜዳው ይገጥማል፡፡

በሌላ በኩል በስፔን ላሊጋ በእግር ኳስ ቤሰብ ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት በሚበቀው የኤል-ክላሲኮ ጨዋታ የሊጉ መሪ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን ምሽት 5፡00 ላይ በኑካምፕ ያስተናግዳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.