የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ119ኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ሲከበር ባደረጉት ንግግር ያሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-
👉 ኢትዮጵያ ጥንታዊ ከሚባሉ ሀገረ መንግሥታት መካከል አንዷ ናት፤ ጠንካራ ተቋማት ከገነቡ ሀገራት ተርታም ትመደባለለች፤ 119 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያ ከገነባቻቸው ተቋማት አንጋፋ የሚባል ነው።
👉 ሠራዊቱ ለ119 ዓመታት ከውጭ ጠላት እና ከውስጥ ባንዳዎች ጋር እየተዋጋ ሀገር አቆይቷል።
👉 የሀገርን ሉዓላዊነት እና አንድነት መጠበቅ የመከላከያ ሠራዊት የተፈጥሮ ባህሪ ነው፤ መከላከያ የሀገረ መንግሥት ስርዓት እና የሀገር መኖር አለመኖርን የሚወስን የህልውና ምሰሶ ነው።
👉 መንግሥትን በመተው የፖለቲካ አንጃ እና ሸማቂ አካላት ተባባሪ መሆን አይችልም፤ ይህን አደረገ ማለት ከተፈጥሮ ባህሪው በመውጣት ሀገር እንድትፈርስ ፈቀደ ማለት ነው።
👉 በዲጂታል ዘመን መከላከያ ሠራዊትን እናፈርሳለን የሽግግር መንግሥት እናመጣለን የሚሉ ደፋር ባንዳዎች ተፈልፍለዋል።
👉 የሀገሪቱን ምሰሶ አፍርሰው ሀገር ለማፍረስ የከጀሉ ደፋር ባንዳዎች በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እየተነዱ እና እየተጫኑ ቋንቋቸው እየተደበላለቀ ገንጣይ እና ሽብርተኛ የባዕድ ተልዕኮ ተሸካሚ ፍጡራን ናቸው።
👉 በዚህ ዓመት መስከረም 13 ከግብፅ፣ ሱዳንና እና ኤርትራ የተቀናጀ ፅምዶ መላላክ የተጠናወተው ህገ ወጡ ህወሓት በሰሜን ወሎ፣ በዋግ እና በአፋር ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ እራሱ በከፈተው ጦርነት እንዳልነበር ሆኗል።
👉 ከምፅዋ ወደብ የተላለፈላቸውን የአንድ መጠነኛ ሀገር የመከላከያ ትጥቅ ሊሆን የሚችል መሳሪያ ሰራዊታችን ተቆጣጥሯል።
የጠላቶቻችን ዱለታ ሲያምራቸው ቀርቷል።
👉 መከላከያ ሠራዊት ተዳክሟል ትንሽ ከገፈተርነው ይፈርሳል ብለው በተነኮሱት ጊዜ ለመከላከያ ሠራዊት የተመኙትን መፈራረስ ፈራርሰው የትግራይን ህዝብ ንብረት ጭነው መንደፈራ ገብተዋል። 4ኛ ዙሩ በዘራችሁ አይድረስ ደርሶባቸዋል።
👉 ህገ ወጡ ህወሓት በዚህ ስምንት ዓመት ውስጥ 4 ትልልቅ ጦርነቶች ከፍቷል፤ ሁሉም ጦርነቶች በበቃኝ የተረቱ ናቸው ነገር ግን መረታቱን ላለመቀበል ስልታዊ ማፈግግፈግ አደረኩ እያለ ሽንፈቱን በፕሮፖጋንዳ ይሸፍናል።
👉 የትግራይ ህልውና፣ የኦሮሞ ህልውና፣ የአማራ ህልውና የሚለው መዝሙር ዋናውን ጠላት ለመደበቅ የተቀበረ መርዝ ነው፤ መርዙን ተሸክሞ የኢትዮጵያ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነው ደግሞ የእኛ ባንዳ ነው።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በእመቤት ሲሳይ