Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙኃን የሕዝብንና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ተዓማኒነት ያለው መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል – ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) መገናኛ ብዙኃን የሕዝብንና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ተዓማኒነት ያለው መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል አሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሐይማኖት ዘለቀ፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ዋና ዳይሬክተሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ማዕከሉ በዘርፉ የሚስተዋሉ የሙያ ክፍተቶችን ለመሙላት እና ጋዜጠኞች ጥልቅ እውቀት እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው።
ሚዲያዎች የሕዝብንና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ሚዛናዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ እንዲያቀርቡ ለማስቻል ማዕከሉ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ማዕከሉ የጋዜጠኝነት እና የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ አቅምን ማጎልበት፣ እውቀት፣ ክህሎት እና የስነ ምግባር ደረጃ ማሻሻል ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ዘርፉን በጥናት እና በስልጠና መደገፍ እንዲሁም የሚዲያ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።
በቅድስት ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.