Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከምስራቅ አፍሪካ አነስተኛ መሣሪያዎች ማዕከል ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የምስራቅ አፍሪካ አነስተኛ መሣሪያዎች ማዕከል (RECSA) ዋና ጸሐፊ ሚስተር ዣን ፒየር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል፣ የናይሮቢ ፕሮቶኮል አፈፃፀምን ለማጠናከር እና የRECSA ኃላፊነቶችን ለማጎልበት ያለመ ነው።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በዚሁ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ የናይሮቢ ፕሮቶኮል የመጀመሪያ መስራች እንደመሆኗ መጠን በRECSA ሴክሬቴሪያት ውስጥ የሚገባትን ተሳትፎ ልታገኝ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሃገር ውስጥ ባለሙያዎች አቅም አዲስ የጦር መሣሪያ መረጃ ቋት ሶፍትዌር አበልፅጎ ወደ ተግባር ማስገባቱን ተናግረዋል።

እንዲሁም የጦር መሣሪያ ምልክት የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ከRECSA ጋር በመቀናጀት መከላከል እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዋና ጸሐፊ ሚስተር ዣን ፒየር ከውይይቱ በኋላ በዋና መሥሪያ ቤት የሚገኘውን የጦር መሣሪያ መረጃ ቋት ሲስተም እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በተመለከቱት ቴክኖሎጂዎች አድናቆታቸውን ገልፀው፣ እነዚህ ተሞክሮዎች ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም መስፋፋት አለባቸው ማለታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለከታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.