ዶናልድ ትራምፕ በጦርነት ወቅት ህይወታቸው ያጡ ወታደሮችን ተሸናፊዎች ብለዋል መባሉ ቁጣን ቀስቅሷል
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጦርነት ወቅት ህይወታቸውን ያጡ የአሜሪካ ወታደሮችን ተሸናፊዎች እና ጥገኞች ብለዋል መባሉ ቁጣን ቀስቅሷል።
ዶናልድ ትራምፕ ወታደሮችን አጣጥለውበታል የተባለው ንግግር አትላንቲክ በተሰኘ መፅህሄት የወጣ ሲሆን አሾሴትድ ፕሬስ እና ፎክስ ኒውስ በዘገባው ላይ በተወሰነ ደረጃ ተሳትፎ አድርገዋል ተብሏል።
ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2018 በፓርስ አቅራቢያ የሚገኝን የአሜሪካ ወታደሮች መካነ መቃብር የተሸናፋች ነው ሲሉ በቦታው ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት መሰረዛቸውን አትላንቲክ የተባለው መፅህሄት ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዝናብ ፀጉራቸውን እንደሚበትንባቸው በመግለፅ እና በጦርነት ወቅት የሞቱትን ወታደሮች መጎብኘት አስፈላጊ እንዳልሆነ በማመናቸው ጉብኝቱን ሰርዘውታል ነው ያሉት አራት የመፅሄቱ ምንጮች።
በተመሳሳይ ጉብኝት በአንደኛው የአለም ጦርነት ወቅት በቤሉዎ ውድ ህይወታቸውን ያጡ 1 ሺህ 800 የአሜሪካ ወታደሮች ጥገኞች ማለታቸውን አትላንቲክ ባወጣው መረጃ ላይ አስፍሯል።
ሆኖም ዶናልድ ትራምፕም ሆኑ አጋሮቻቸው የወጣውን ዘገባ አጣጥለዋል።
ይህ የአትላንቲክ መፅህሄት መረጃ በወታደር ቤተሰቦች በተለይ ህይወታቸወነ በጦርነት ወቅት ባጡ ወታደሮች ቤተሰቦች ላይ ቁጣን ቀስቅሷል።
ለረጅም ጊዜ በወታደርነት ያገለገሉ ቡድኖችም ይህን የዶናልድ ትራምፕ አስተያየት በመቃወም ቀዳሚ ሆነዋል።
ይህ ሁኔታ በመጪው ጥቅምት ወር በአሜሪካ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ትራምፕ የወታደሮችን እና የቤተሰቦቻቸውን ድምፅ እንዲያጡ ሊያደርግ እንደሚችል ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛ።
ነጩ ቤተመንግስት በ2018 ባወጣው መግለጫ ጉብኝቱ የተሰረዘው በመጥፎ የአየር ሁኔታ ሄሊኮፕተራቸው በማረፉ ነው ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።