Fana: At a Speed of Life!

ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከኮፕ31 ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከህፃናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬት ሃምፕተን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ውይይቱ ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር እንደመሆኗ በትብብር ዕድሎች፣ በቆሻሻ አያያዝና አጠቃቀም፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምና የከተሞች ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል።

ዘላቂ፣ አረንጓዴና አካታች የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የተሻለችና ዘላቂ ከተማ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሠራለን ነው ያሉት።

#ኢትዮጵያ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #COP31 #COP32 #COP32ETHIOPIA
#fanamediacorporation

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.