የተገበርነው ማሻሻያ ችግሮችን ተቋቁመን እንደ ሀገር እንድንጸና አግዞናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገበርናቸው ማሻሻያዎች ኢኮኖሚያችን ችግሮችን ተቋቁሞ እንደ ሀገር እንድንጸና አግዞናል አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተገበረቻቸው ማሻሻያዎች ኢ-ተገማች በሆኑ አደጋዎች ውስጥ የማለፍ አቅም ለመፍጠር ማስቻሉን የተለያዩ አመላካቾችን በማቅረብ አስረድተዋል፡፡
በዓለም ላይ አሁን ያለው ጂኦፖለቲካዊ ውጥረትና ግጭት በዋናነት የንግድ ስርዓት እንዲዛባ ማድረጉን ገልጸው፤ ይህም በዓለም እድገት ላይ ተጨባጭ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል ነው ያሉት፡፡
የንግድ መስመሮች መታወክ አንዱ ችግር መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገራት ከውጭ ገዝተው የሚያስገቧቸውን ግብዓቶች በሚገልጉት ጊዜ እንዳያገኙ እክል እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንደ ነዳጅና ማዳበሪያ ያሉ መሰረታዊ ምርቶች እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ማጋጠሙን ገልጸው፤ ይህም ባደጉ ሀገራት ጭምር የኑሮ ውድነትና የእድገት መንገራገጭ አስከትሏል ብለዋል፡፡
በዚህ መነሻነት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በዚህ ዓመት የዓለም አማካይ እድገት የዓለም እድገት ከ3 ነጥብ 1 በመቶ እንዲሁም ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ከ4 ነጥብ 3 በመቶ እንደማይበልጥ ግምት ማስቀመጡን አንስተዋል፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገበረቻቸው ማሻሻያዎች ኢኮኖሚዋ ችግሮችን ተቋቁሞ እንደ ሀገር እንድንጸና አግዞናል ነው ያሉት፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በኃይለማርያም ተገኝ