Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያን ባሉበት ፖስፖርትና መታወቂያ ማሳደስና መረከብ የሚችሉበት ስርአት ተግባራዊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ወደ ኤምባሲ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው ፖስፖርት እና የትውልድ ኢትዮጵያን መታወቂያ (Origin ID) ማሳደስና መረከብ የሚችሉበት ስርአት በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረ።

ስርዓቱን የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ቪዲቸር ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው።

በስርአቱ የሚጠቀሙ ተገልጋዮች የታደሰ ፓስፖርት ወይም ትውልድ መታወቂያ በ15 ቀን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪም ወደ ኤምባሲ በመመላለስ የሚያጠፉት ግዜና ወጪ አይኖርም።

የተዘረጋው ስርዓት ለ6 ወር በሙከራ የሚቆይና ያመጣው ለውጥ የሚገመገም ሲሆን፥ ውጤቱ ታይቶ በሌሎች ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.