Fana: At a Speed of Life!

ሚንስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለም-ፀሀይ የአርባ ምንጭ ሆስፒታልና የኮቪድ-19 ሕክምና ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ከተማ ሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ጎብኙ፡፡

እንዲሁም በኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ተገኝተው ያለውን የስራ እንቅስቃሴ መመልከታቸውም ተገልጸል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በጉብኝቱ ወቅት የህክምና ተቋማቱ ለአካባቢ ነዋሪዎች እየሰጡ ያለውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እና ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመከላከልና የመቆጣጠር ምላሽ አሠጣጥ የሚበረታታና ውጤታማ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ለማዕከሉ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የተቋማቱ ስራ ኃላፊዎችም ከሚኒስትር ዴኤታዋ ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

ኃላፊዎቹ አገልግሎታቸውን በተሟላ መንገድ ለመስራት አያስችሉንም ያሏቸውን ጉድለቶች አንስተው ውይይት አድረገውባቸዋል፡፡

የህክምና ተቋማቱ ያሉበት የስራ አፈጻጸም የሚበረታታ ቢሆንም ለተሻለ ስራ መነሳትና የጤና አገልግሎቱን ይበልጥ ማሻሻል ያስፈልጋል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታዋ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.