Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰአታት 892 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ8 ሺህ 254 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 892 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ 17 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ሚኒስትሯ በገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 245 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም 710 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 35 ሺህ 670 ደርሷል፡፡
ከዚህ ባለፈ እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 255 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 321 ሺህ 164 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 80 ሺህ 895 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ቁጥር 35 ሺህ 670ቱ ከቫይረሱ ሲያገግሙ 43 ሺህ 968 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ አለባቸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.