Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአየር ንብረት ተጋላጭነት ፎረም የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአየር ንብረት ተጋላጭነት ፎረም የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳተፉ፡፡

የፎረሙ ፕሬዚደንት በሆኑት የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የተጠራው ስብሰባ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ለዚህም ተገቢውን እንቅስቃሴ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡበት ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዚህ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ጊዜ እንደሌለ ጠቅሰው፥ ሃገራት ባላቸው አቅም ሁሉ እስከ ታህሳስ 2013 ዓ.ም. ድረስ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ሳይደርስ ምላሽ መስጠት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ይህ ቀነ ገደብ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃውን እና እየባሰ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ለማስቆም የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በፓሪስ ስምምነት ላይ የሰፈረውን የ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴሊሺየስ ግብ ለማሳካት ይረዳል ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.