በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራው ከፍተኛ የህብረቱ ልዑክ ሶማሌ ክልል ገባ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ የተመራው ከፍተኛ የህብረቱ ልዑክ ሶማሌ ክልል ገብቷል።
ልዑኩ ጅግጅጋ ከተማ ሲደርስ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድና በሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።
ከዚህ ባለፈም አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በክልሉና በሀገሪቱ ስለተከናወኑ ሥራዎች ለህብረቱ ልዑክ ገለፃ አድርገዋል።
በዚህም ባለፉት ሁለት አመታት በክልሉ ሰብዓዊ መብት ጥበቃ፣ በሰላምና ፀጥታ፣ በጤና፣ ትምህርት፣ በሥራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስለተከናወኑ ስራዎች ለልዑኩ ገለፃ ተደርጓል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና ምክትል ፕሬዚዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ በበኩላቸው በርዕሰ መስተዳድሩ በተደረገላቸው ገለፃ ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በክልሉ የተፈጠረው ለውጥ የሚደነቅ እንደሆነና የህብረቱ እገዛ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።