የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፀጥታ ፣ የደህንነት እና ባለ ድርሻ አካላት ልዩ የምስጋናና እውቅና መርሃ ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 1 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘንድሮው የመስቀል እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ልዩ እውቅና መርሃ ግብር አካሄደ።
የምስጋና እና የእውቅና ዝግጅቱ በቅርቡ በተመረቀው ፕሮግራም ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።
የዘንድሮው የመስቀል እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፀጥታ፣የሀይማኖት ተቋማት ፣የሚዲያ አካላት እና የባለድርሻ አካላት የምስጋና እና የእውቅና መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ፣ሚኒስትሮች ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የፀጥታ፣ የደህንነት እና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በዘቢብ ተክላይ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።