ባለፉት 24 ሰዓታት 866 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 383 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 866 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 84 ሺህ 295 ደርሷል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ አማካኝነት የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 287 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ 633 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 38 ሺህ 316 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
እንዲሁም 271 ሰዎች ፅኑ ህሙማን ማዕከል ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።