ዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን ተከበረ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን ተከብሮ ውሏል።
ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ11ኛ ጊዜ “የተጠናከረ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ለህዝብ ልማትና ዕድገት” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።
በዓሉ የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በበይነ መረብ በመታገዝ ነው የተከበረው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የድርጅቱ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ልዩ ፀሀፊ ተወካይ ማሚ ሚዙቶሪ ቀኑን አስመልክቶ በተንቀሳቃሽ ምስል ያስተላለፉት መልዕክት ለውይይቱ ተሳታፊዎች ቀርቧል።
የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የስራ ሀላፊዎችም መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
በውይይቱ በኢትዮጵያ በአደጋ ስጋት ቅነሳ እና አደጋን ቀድሞ ከመከላከል አኳያ እየተከናወኑ ያሉት ስራዎችን አስመልክቶ የመነሻ ፅሁፎች ቀርበዋል።
በቀረቡት ፅሁፎች ላይ ውይይት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል ።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።