Fana: At a Speed of Life!

ባለሥልጣኑ በ2 ቢሊየን ብር ወጪ 55 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማልማት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተያዘው በጀት አመት በ2 ቢሊየን ብር ወጪ 55 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በማልማት 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማምረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
 
የባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
እስከ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስም ዘጠኝ ጉድጓዶችን በማልማት በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደ ስርጭት ገብቷል ብለዋል።
 
ኢንጂነር ዘሪሁን ቀሪ 80 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ እስከ በጀት አመቱ ማብቂያ ድረስ ወደ ስርጭት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
 
ዋና ስራ አስኪያጁ በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
 
ነገር ግን ከኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ በተወሰኑ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ አቅርቦት ችግር እንደተፈጠር መናራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
በዚህም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በመብራት መቆራረጥ ምክንያት 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውኃ ማምረት አለመቻሉን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ ከተመረተው 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውኃ ውስጥ ህብረተሰቡ ጋር ሳይደርስ ቀርቷል ብለዋል፡፡
 
ችግሩን ለመፍታትም የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመነጋገር
የውሃ አቅርቦቱን ለማስተካከል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.