የህዳሴ ግድብ ለህዝባዊ አንድነትና የኢኮኖሚ ግንባታ ያለውን ሚና ለማሳደግ እንደሚሰሩ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግንባታና ህዝባዊ አንድነት ያለውን ሚና ለማሳደግ እንደሚሰሩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ።
ዋና ዳይሬክተሩ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትና የአንድነት መጠናከር አይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልም የሁሉም ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታልም ነው ያሉት።
በተለይም በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሃገራቸው ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ሁለንተናዊ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
በውጭ ያለውን አቅም በማቀናጀት እስካሁን በቂ ስራ አለመከናወኑን ጠቁመው ÷ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ አውስተዋል።
በሃገር ውስጥ በሚፈጠሩ የተለያዩ የፖለቲካ ልዩነቶች ምክንያት በውጭም ይሁን በሃገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ሳይከፋፈሉ ለሃገራዊ ልማትና እድገት በጋራ መቆም ይኖርባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።