Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል በኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች የቀረበውን ጥሪ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል በኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች የቀረበውን ጥሪ መቀበላቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ÷ ማክሰኞ ኅዳር 8 ቀን 2013 ዓም “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል ርእስ የ2 ደቂቃ ፕሮግራም እንዲኖር በኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች የቀረበውን ጥሪ እኔም ተቀብያለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።
በጥሪው እንደተገለፀው ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 5:30 ላይ የሚደረግ ነው ተብሏል።
በሰዓቱ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በያሉበት ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ያላቸውን ክብር ይገልፃሉ።
ለአንድ ደቂቃ የመቆም ሥርዓቱ ሲጠናቀቅ በቀጣዩ አንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ ያጨበጭባሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥነ-ሥርዓትቱን ሕብረተሰቡ በየአካባቢው፣ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየድርጅቱና በየቤቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን የበኩሉን እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.