ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀጨኔ የሴት ህጻናት ማቆያና ማቋቋሚያ ተቋም የሚገኙ ህጻናትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ቀጨኔ የሴት ህጻናት ማቆያና ማቋቋሚያ ተቋም የሚገኙ ህጻናትን ጎብኝተዋል፡፡
ምክትል ከንቲባዋ እንዳሉትም ለህጻናት ፍቅር ልናሳያቸው፣ ልንንከባከባቸው፣ በመልካም መንገድ ልንመራቸው፣ ልናስተምራቸው እና የመልካም ራዕይ ባለቤት ልናደርጋቸው ይገባል እንጂ ለጦርነት ፣ለጥላቻ እና ለክፋት ልንማግዳቸው አይገባም ።
ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በማቆያው ለሚገኙ ህጻናት የትምህርት መርጃ መሳሪያ እና የንፅህና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡