በህግ ማስከበርና ዘመቻው በምዕራብ ግንባር ተገኝተው ሲዘግቡ ለነበሩ የሚዲያ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ በምዕራብ ግንባር ተገኝተው በመዘገብ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለተወጡ የሚዲያ ባለሙያዎች የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ::
በዘመቻው በምእራብ ግንባር ከዳንሻ፣ ሁመራ፣ ሽራሮ፣ በሽሬ አድርጎ እስክ አድዋና አክሱም የዘለቀ ስምሪት ለነበራቸው የሚዲያ ባለሙያዎች ነው የምስጋና መርሃ ግብሩ የተካሄደው።
በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የአገር መከላከያ ሰራዊት ተወካዮችና የተለያዩ የሚዲያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዚሁ ጊዜ፥ በስፍራው የተገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች በህግ ማስከበር ዘመቻው ዙሪያ ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ በማድረስ በዘመቻው ዙዩያ የነበሩ ብዥታዎች እንዲጠሩ ማድረጋቸውን አንስተዋል።
በአሁኑ ጊዜም በተለያዮ ግንባር የሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች በህግ ማስከበር ዘመቻው ዙሪያ ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ በማድረስን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፥ በዛሬው እለት የተካሄደው የእውቅና ስነ ስርዓት ለቀጣይ ስራቸው አቅም እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።
ከዚህ በዘለለ ግን በዘመቻው ወቅት የሀገር መከላከያ ዘንድ ያለውን እስከ መስዋዕትነት የዘለቀ የሀገር ፍቅር መመልከት የቻሉበት እድሆነም አስታውሰዋል።
ተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡–
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!