Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ እና አፋር ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ሲካሄድ የቆው የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሶማሌ እና አፋር ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር  በአዳማ ከተማ ሲካሄድ  የቆው  የምክክር መድረክ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገር ሽማግሌዎች ትስስር ከሰላም ሚኒስቴር እና ከጀሰቲስ ፎር ኦል. ፒ. ኤፍ. ኢትዮጲያ ጋር በመታባበር በአፋር እና ሶማሌ ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ለሁለት ቀናት በአዳማ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

በውይይት መድረኩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል።

መድረኩ “ህብረ-ብሄራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ውስጣዊ ችግሮቻችንን በምክክር እንፍታ!” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው

በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ለሚነሱ ግጭቶች መነሻ ችግሮች እና የመፈትሄ ሀሳቦች ላይ ሰፊ  ውይይትና ክርክር በማድረግ ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በአቋም መግለጫቸው ላይ በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ሰላም ማስፈን እና ከሁለቱም ክልሎች የተወከሉ ሽማግሌዎች  ከሁለቱ ክልል መንግሥታት እና ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመነጋገር ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ተስማምተዋል።

እንዲሁም  ያላግባብ የታሰሩ እስረኞችን ለመፍታት፣ አዳዲስ ሰፈራዎች ለጊዜው ለማስቆም፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ለመመለስና  መልሶ ማቋቋም እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያ ህዝብን የሚያጋጩ ተረኮች እንዲቆሙ ለማድረግ  መስማማታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.