Fana: At a Speed of Life!

በጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኡማሮ ሲሶኮ አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የጊኒ ቢሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ማሸነፋቸው ተነገረ።

የ47 ዓመቱ ኢምባሎ ተቀናቃኛቸው ዶሚንጎስ ሲሞዬስ ፔሬራን በምርጫው አሸንፈዋቸዋል።

ተቀናቃኛቸው ፔሬራ የምርጫው ውጤቱ የተጭበረበረ ነው በሚል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ገልጸዋል።

የምርጫ ታዛቢዎች በበኩላቸው ምርጫው ላይ የድምፅ ማጭበርበርን የሚያመላክት ምንም ማስረጃ አላገኘንም ብለዋል።

ኢምባሎ ከውጤቱ በኋላ በጊኒ ቢሳው ያለውን ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ድህነትን ጨምሮ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርና ያልተረጋጋው የሃገሪቷ ፖለቲካዊ ሁኔታ ግን ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ፈታኝ ሊሆንባቸው ይችላል ተብሏል።

ኢምባሎ ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2018 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.