Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለኢፈርት ድርጅቶች ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለኢፈርት ድርጅቶች ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር መሾሙን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

ከፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዉጣጣ የምርመራ ቡድን በኢፈርት ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ እያካሄደ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ከዚሁ የወንጀል ምርመራ ጎን ለጎን የሀብት ጥናት እና ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን የድርጅቶችን ንብረት የማሸሽና ማባከን ተግባራትን ለመከላከል ሕግ በሚፈቅደዉ አግባብ ጊዜያዊ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ ስለነበረበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት የዕግድ አቤቱታ በማቅረብ የድርጅቶቹ የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ፣ ሌሎች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እንዳይሸጡና እንዳይለወጡ፣ በሌላ ማንኛዉም መንገድ ወደ ሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ማሳገዱ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ድርጅቶችን ወደ ሥራ ማስገባት፣ በእያንዳንዱ ድርጅት ዉስጥ ተቀጥረዉ ከሚሰሩ ብዛት ያላቸዉ ሠራኞች የሥራ ዋስትና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍና የድርጅቶቹን ንብረት ከብክነት በመከላከል በአግባቡ ጠብቆ ለመያዝ ያመች ዘንድ የወንጀልና የሃብት ምርመራዉ ተጠናቆ በጉዳዩ ላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅራቢነት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመ/ቁ 263499 በታህሳሰ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ሰባት አባላት ያሉት ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾሟል፡፡

በዚህም መሠረት ባለአደራ አስተዳደሩ በፍርድ ቤት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት የማስተዳደር ሥራን የሚያከናዉን ሲሆን

በየጊዜዉ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሾመዉ ፍ/ቤት እንዲሁም ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡

የጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደሩ አባላት ገለልተኝነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የሙያ ሥነ ምግባር እና የነዚህን አይነት ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት፣ በቦርድ አመራርነት እንዲሁም አባልነት በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆናቸዉን ከግምት ዉስጥ በማስገባት የተመረጡና የተሾሙ ናቸዉ፡፡

ለኢፈርት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለ አደራ አስተዳደር በማሾም ሂደት ውስጥ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዳስትሪ ሚኒስቴር እና የትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍና አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከፍተኛ አመራሮችም ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ስራውን ሲመሩ እና ሲከታተሉ መቆየታቸውን በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አለምአንተ አግደው ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.