Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤ ፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር ማዋል ጀምሯል፡፡

በዞኑ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር እጃቸው ያለበትን፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ ሲሆን እስካሁንም 5 አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዚህም፡- መሠረት

1ኛ. አቶ ቶማስ ኩዊ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ

2ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

3ኛ. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡- የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

4ኛ. አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ

5ኛ. አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

እነዚህ አመራሮች ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የክልሉ መንግስት በዞኑ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ሲሆን፣ ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተሳትፎ ባደረጉ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብሏል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ወደ ሠላም ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲደግፍ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.