ተጨማሪ 351 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 6 ሰዎች አገግመዋል
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 96 ሰዎች የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ተደርጎ 351 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ተጨማሪ 351 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 6 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 120 ሺህ 989 መድረሱንም አስታውቋል።
ከቫይረሱ 1 ሺህ 6 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 105 ሺህ 824 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።
ከዚህ ባለፈም በቫይረሱ የስድስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 870 ደርሷል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!