በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣት ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ፎረም ምስረታ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣት ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ፎረም ምስረታ መካሄዱን ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተገኙበት ነው የወጣት ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ፎረም ምስረታው የተካሄደው።
ሚኒስትር ዲኤታዋ የወጣቶችን ጥያቄ ለመመለስ፣ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እና የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደ ሃገር ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የፎረሙ መመስረቻ ረቂቅ መመሪያ ለውይይት ቀርቦ የሚፀድቅ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዲኤታዋ በሚመሰረተው ፎረም ውስጥ ወጣቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ጀኔራል ወይዘሮ አልማዝ ገበያው ወጣቶች በሚካሄደው የፎረም ምስረታ ስብሰባም ሆነ በቀጣይ የፎረሙ ዓላማ ግብ እንዲመታ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲበረክቱ መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!