Fana: At a Speed of Life!

ለሰላምና ልማት እንጂ ለኦነግ ሸኔ ቦታ የለንም- የደምቢዶሎ ከተማ ህዝብ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለም ወለጋ ዞን የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ኦነግ ሸኔን የማደን ዘመቻ አካሄዱ፡፡

የአሰሳ ስራው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየ መሆኑን የደምቢዶሎ ከተማ ኮሙኒኬሽን ገልጿል፡፡

ዘመቻውን ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሙላቱ ለሊሳ በአካባው በቡድኑ ሲፈጠር የቆየውን የፀጥታ ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ነዋሪዎች ቡድኑን ለማስወገድ የድርሻቸውን በመወጣት የከተማዋን ፀጥታ መጠበቅ እንዳለባቸውም አስረድተዋል፡፡

ህዝቡ ከመንግስት ጋር በመተባበር ሰላሙን ማስጠበቅ ይገባዋል ብለዋል ከንቲባው፡፡

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ ጉርሜሳ በዘመቻው ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ የኦነግ ሸኔ ሽፍቶችን በማደን ለህግ ለማቅረብ በሚሰራው ስራ ተባባሪ መሆኑን መቀጠል ይገባዋል ነው ያሉት፡፡

እነዚህ የጥፋ ተላላኪዎች ልክ እንደ አለቆቻቸው የህወሓት ጁንታ የትም ቦታ እንዳይኖራቸው የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

መንግስት ህግ ለማስከበር በሚሰራው ስራ ህዝቡ ድጋፉን እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዘመቻው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአካባያቸው ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍን ቡድኑን ለማስወገድ በሚሰራው ስራ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ከተማቸው ከዚህ በኋላ ለሰላምና ለልማት እንጂ ለኦነግ ሸኔ ቦታ እንደማይኖራት ገልፀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.