Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ህብረተሰቡ ሀይማኖታዊ በዓላትን ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲያከብር አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላትን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲያከብር የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ በዓላቱን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሳእረላ አብዱላሂ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር አሁን ላይ እየጨመረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው በዓላት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም በተለይም በአመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ፣ የገና እና የጥምቀት በዓላት አከባበር ላይ፥ ምዕመኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያከብር መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጉባኤው ወደቤተ እምነቶች የሚመጡ አማኞች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ እና የየቤተ እምነቱ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም ምዕመኑ በየትኛውም ሁኔታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና ንክኪን በመቀነስ እንዲሁም ንጽህናን በመጠበቅ የቫይረሱን ስርጭትና ያለውን ተጋላጭነት እንዲቀንስም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ተጨባጭ የጤና ችግር መሆኑን በመረዳት ለአፍታም ቢሆን መዘናጋት አይገባምም ነው ያለው፡፡

በማህሌት ተክለብርሃን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.