ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ˝በከተማችን፣ በሀገራችን እና በመላው ዓለም የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም እንኳን “˝ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል˝” በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
በተለይም በዚህ ከቤተሰብ፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር በአብሮነትና በጨዋታ በሚከበር በዓል ላይ በስራ ገበታቸው ሆነው ለሚያከብሩ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን መልካም የገና በዓል እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ምክትል ከንቲባዋ ህዝቡ በዓሉን ሲያከብር አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የኮቪድ -19 ወረርሺኝ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!