አምባሳደር ሂሩት ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ዋና ፕሮቶኮል ኃላፊ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ አቀረቡ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም ብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በአውሮፓ ህብረት ተቋማት ኢትዮጵያን መወከል የሚያስችላቸውን የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ለአውሮፓ ኮሚሽን ዋና የፕሮቶኮል ሃላፊ ኒኮላስ ደ ላ ግራንድቪል አቀረቡ፡፡
አምባሳደሯ እና የፕሮቶኮል ዋና ሃላፊው በኤምባሲው እና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
አምባሳደር ሂሩት በአውሮፓ ህብረት ተቋማት ኢትዮጵያን መወከል የሚያስችላቸውን የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ነው ለአውሮፓ ኮሚሽን ዋና የፕሮቶኮል ሃላፊ ኒኮላስ ደ ላ ግራንድቪል ያቀረቡት፡፡
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ግንኙነት ከመሰረቱ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እንዳሳለፉ ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!