Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓል እና አዲስ አመትን በትናንትናው ዕለት ያከበሩት የጋሞ ዞን የደረማሎ ወረዳ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመስቀል በዓልም በመስከረም ወር በታላቅ ድምቅት ይከበራል።

ነገር ግን በዞኑ በደረማሎ ወረዳ የጮዬ ሰዴ ደሬዎች የመስቀል በዓል እና አዲስ አመትን የሚያከብሩት በራሳቸው የቀን አቆጣጠር ቀመር መሰረት ነው፡፡

ለሀገሪቱ ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት ፀሎትና ምህላ የሚደረግበት በዓል መሆኑን የተናገሩት ካዎ ታደሰ በልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የተቀያየሙ ሰዎች እርቅ ፈፅመው ወደ አዲስ ዓመት የሚሸጋገሩበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የጋሞ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ እያሱ እሸቱ በዞኑ 42 ደሬዎች (ግዛት) አስተዳዳሪዎች እንደሚገኙ ናገራሉ፡፡

ከእነዚህ ደሬዎች ውስጥ በደረማሎ ወረዳ የሚገኙት የጮዬ ሰዴ ደሬዎች የመስቀልን በዓል ሸኝተው አዲስ አመትን በድምቀት በትናንትናው ዕለት ተቀብለዋል፡፡

እንደ አቶ እያሱ ገለጻ የጋሞ ደሬዎች የመስቀልን በዓል ከነሀሴ ወር ጀምሮ ማብሰር ይጀምራሉ ይህ ደግሞ መስቃላ ሞይዞ ወይንም መስቀልን መሸኘት እንደማለት ነው፡፡

በዘንድሮው በዓል የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው በከፍታው በሚታወቀው የጉጌ ተራራ ላይ  የገና ጨወታ በመጫወት የበዓሉ ተሳታፊ መሆናቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ልዩ ልዩ የአደባባይ ላይ ትርኢት በማሳየት ደመራ በመለኮስ እና ወደ አዲስ አመት መሸጋገርን በማብሰር የበዓሉ አከባበር ተጠናቋል ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.