በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነቡት የደባርቅ ብርሃንና የዋግ ኽምራ ሳህላ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡት የደባርቅ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ እና የዋግ ኽምራ ሳህላ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመረቁ።
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ፣የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞ እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ትምህርት ቤቶቹ ተመርቋል።
የደባርቅ ብርሃን ትምህርት ቤት መሰረተ ድንጋይ ባለፈው ግንቦት ወር ተጥሎ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበት ግንባታው መጠናቀቁ ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ የዋግ ምህራ ሳህላ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበት የተገነባ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሁለቱም ትምህርት ቤቶች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ በአንድ ፈረቃ 1 ሺህ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አላቸው ተብሏል።
ትምህርት ቤቶቹ በውስጣቸው የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አካተዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ተማሪዎች እና ወላጆች ይህን እንድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የደባርቅ እና የዋግ ኽምራ አካባቢዎች በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የትምህርት ቤት እጥረት የሚታይባቸው በመሆኑ ፅህፈት ቤቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የገነባው ትምህርት ቤት ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ትውልድን የሚያሻግር ስራ ከህዝብ የወጡ መሆኑን በተግባር ያሳዩበት በመሆኑ የአማራ ክልል ክልል መንግስት ለቀዳሚት እመቤቷ ከፍተኛ ክብር ይሰጣል ብለዋል።
ትምህርት ቤቱ በአጭር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በጥራት የተገነባ በመሆኑ እኛም ይሄን ተሞክሮ ወስድን እንደ ክልል ትምህርት ቤቶችን በጥራት በፍጥነት የምንገነባ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።።
በአማራ ክልል በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት አራት ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።
በፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!